ኪንታሮት (Hemorrhoids)
ኪንታሮት (Hemorrhoids) አንዳንዴ :በእንግሊዝኛ ( piles), በምንፀዳዳበት አካላችን ላይ ወይም ውስጥ ያሚያብጥ :የደም :ስር : ማለት ነው ከ(varicose veins) ጋር የሚመሳሰል ባህሪ አላቸው :: varicose vein በእግር ላይ የምያብጥ የደምስር :ሲሆን ኪንታሮት በመፀዳጃ አካላችን (anus/ፊንጢጣ )ላይ ያምያብጥ : የደም ስር ነው::

የኪንታሮት :በሽታ :በተለያዩ :ምክንያት :ቢከሰትም :የምከሰትበትን :ምክንያት :ማወቁ :ወይም ይህ :ነው :ለማለት ይከብዳል ።ስለዚህ በአብዛኛው :መነሻው :አይታወቅም ።
ቢሆንም :የሆድ :ድርቀት : ወይም :በእርግዝና :ጊዜ :የሚፈጠረው :ግፊት :የበሽታው መንስኤ :ሊሆን እንደሚችሉ ይገመታል ። ኪንታሮት ውስጥ ወይም ውጭ የመፀዳጃ አካል(anus/ፊንጢጣ) ላይ ሊከሰት :ይችላል:
ኪንታሮት ከአራት ሰው መሃል በሶስቱ (75 ፐርሰንቱ ሕብረተሰብ ) ላይ ከጊዜ ወደጊዜ ሊከሰት የሚችል ሲሆን አንዳንዴ በፍፁም ምልክት ላያሳይ እና በሌላ ጊዜ ደግሞ ልያም፣ሊያሳክክ ፣ምቾት ሊያሳጣና እና ሊደማም ጭምር ይችላል ።
አልፎ አልፎ በኪንታሮት ውስጥ የደም መርጋት ሲፈጠር:አደገኛ :ባይሆንም : በጣም ሊያም ይችላል:ይህ ሲሆን :በባለ ሙያ :ተከፍቶ ደሙን :ማፍሰስ የግድ የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል። ።ቢሆንም ሌሎች የተሻሉ አማራጮች የተሻለ ውጤት ሊያስገኙ ይችላሉ አንዳንዴ የአኗኗር ዘይቤያችን በመቀየር እና ቤት ውስጥ በሚገኙ ግብአቶች ሕክም ህመሙን ለማጥፋት ይቻላል ።

[recentvideo]

ምልክት (Symptoms)
የክንታሮት :ህመም :የሚከተሉትን:ልያጠቃልል:ይችላል ::
የለምንም :ህመም :በሰገራ ላይ ወይም : በተጠቀምንበት :ሶፍት :ላይ :ደም :ማየት
ፊንጢጣ:አከባቢ :የማመም:የማቃጠል እና የማሳከክ ስሜት
ህመም እና ምቾት ማጣት
ፊንጢጣ አከባቢ ማበጥ
ፊንጢጣ ላይ የሚወጣ በጣም የሚያም እብጠት ( thrombosed hemorrhoid) ወይንም የረጋ ደም የልበት ኪንታሮት ቀድሞ እንደተጠቀሰው ።
የኪንታሮት ህመም ምልክት እንደወጣበት ቦታ ይለያያል
ውስጥ የሚወጣ (Internal hemorrhoids).
ይህ አይነቱ ኪንታሮት የማይታይ ወይም ህመም የሌለው ሲሆን ነገር ግን በምንፀዳዳበት ወቅት ምቾት ሊያሳጣ ወይም ኪንታሮቱ ስለሚጫጫር :ሊደማ :ይችላል ።
አንዳንዴ ስንፀዳዳ ተገፍቶ ወደ ውጪ ሊወጣ ይችላል ይህ ሲሆን (prolapsed hemorrhoid)ይባላል ።
ውጭ የሚወጣ (External hemorrhoids ) –
እንዲህ አይነቱ ኪንታሮት በፊንጢጣ ዙሪያ ከቆዳ ስር የሚወጣ ሲሆን ሲነካካ ሊያም፣ሊያሳክክ እና ሊደማ ይችላል ።
ውስጡ ደም የረጋ (Thrombosed hemorrhoids) ውጭ የሚወጣው ኪንታሮት ውስጡ ደም ሲረጋ ጠጣር እብጠት ወይም ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር እባጭ ይሆናል ።

ስንፀዳዳ የሚደማ ከሆነ በአስቸኩአይ ሐኪምቤት በመሄድ በሽታው ለከፋ ደረጃ ሳይበቃ ማስቆም አለብን ምክንያቱም ይህ የኪንታሮት ዋነኛው ምልክት ስለሆነ ። በተለይ ዕድሜያችን ከ 40 ዓመት በላይ ከሆነ የፊንጢጣ መድማት በሌሎች በሽታ ሊከሰት ስላሚችል ሐኪማችሁን ተገቢውን ጥያቄ መጠየቅ ይገባል ። ከደም መፍሰስ ጋር ተያይዞ የማዞር ወይም ራስ መሳት ከተፈጠረ :በአስቸኩአይ :ወደሃኪም :ቤት :መሄድ :የግድ :ይላል ።


መነሾ (Causes)
በ ፊንጢጣ አከባቢ ያሉት የደም ስሮች በምንፀዳዳበት ሰዓት የመሳብ እና የመለጠጥ ሁኔታ ስለሚፈጠር :የደምስራችን ልያብጥ ይችላል : ያበጠው የደም ስር :ኪንታሮት ይባላል :ይህ እብጠት :እንደተባለው:በ ፊንጢጣ አካባቢ በሚፈጠር በግፊት ነው ምክንያቶቹም የሚከተሉት ናቸው ።
በምንፀዳዳበት :ወቅት :የሚፈጠር ግፊት
ሽንት ቤት ላይ ለረጅም ሰዓታት መቀመጥ
ለርጅም ጊዜ የሚቆይ ተቅማጥ እና የሆድ ድርቀት
ውፍረት
እርግዝና
ግብረ ሰዶም
ዝቅተኛ (fiber ) ምግብ
ዕድሜያችን በገፋ ቁጥር እና በእርግዝና ሰዓት በፊንጢጣ አከባቢ ያሉት የደምስሮች ስለሚዳከሙ:ለኪንታሮት በሽታ የመጋለጥ እድላችን የሰፋ ነው።
የኪንታሮት ህመም ሊያመጣ የሚችለው ችግሮች (Complications)
ብዙውን ጊዜ ባይከሠቱም የሚከተሉት ናቸው
የደም ማነስ
የደም ስሮች ስለሚተሳሰሩ እብጠቱ ላይ የደም መርጋት ሊፈጠር እና ለከፋ ህመም ሊያጋልጥ ይችላል።
መከላከያ (Prevention)
ዋነኛው ኪንታሮት የምንከላከልበት መንገድ ሰገራችን እንዳይደርቅ ማድረግ እና በቀላሉ መፀዳዳት መቻል ነው ።
አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
ብዙ ፈሳሽ መጠጣት
በምንፀዳዳበት ሰዓት እራስን አለማጨናነቅ ወይም ግፊት አለመፍጠር
እንደመጣን ቶሎ ብሎ መፀዳት
የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ እና ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ ናቸው

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.